This page contains information about Alcoholic Beverage Regulation Administration services for Amharic speakers.
የኤጀንሲው ስም፡ የአልኮል መጠጥ ቁጥጥር አስተዳደር (ከዚህ በኋላ ABRA ተበሎ ይጠራል)
ተለዕኮ:
የአልኮል መጠጥ ቁጥጥር አስተዳደር (ABRA) ተለዕኮ የአልኮል መጠጦችን ሽያጭና ማከፋፈል በመቆጣጠር የህዝብን ጤና፣ ደህንነትና ምቾት መደገፍ ነው።
አገልግሎቶች:
ABRA ፈቃድ የተሰጣቸውን፣ ህግ አስፈጻሚ ኤጀንሲዎችን፣ የአካባቢ አማካሪ ኮሚሽኖችን (ANC)፣ የማህበረሰብ ተቋማትን እንዲሁም አጠቃላይ ህብረተሰቡን ፈቃድ በመስጠት፣ በማሰልጠን፣ ውሳኔ በማስተላለፍ እና ማህበረሰቡን በመድረስና ህግን የማስከበር ጥረቶችን በማከናወን ሁሉም አካላት የዲስትሪክቱን ህጎች፣ ድንጋጌዎች እንዲሁም የABRA ፖሊሲዎችን እና ደንቦችን እንዲረዱና እንዲከተሉ ያደርጋል።
አብይ ፕሮግራሞች:
ABRA በሚከተሉት አምስት ፕሮግራሞች ውስጥ ሥራውን ያከናውናል፡ (1) ውሳኔ መስጠት፣ (2) የኤጀንሲ አስተዳደር፣ (3) ምርመራዎች፣ (4) ፈቃድ መስጠት እና (5) የመዝገቦች አስተዳደር።
- ውሳኔ መስጠት - ለአልኮል መጠጥ እና ቁጥጥር (ABC) ቦርድ ዕርምጃዎችና የዳኝነት ችሎቶች አስተዳደራዊ ድጋፎችን ይሰጣል።
- የኤጀንሲ አስተዳደር - ፕሮግራማዊና ተግባራዊ ውጤቶችን ለማከናወን የአስተዳደር ድጋፍና አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችን ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም በውጤት ላይ ያተኮረ በጀት ለሚጠቀሙ ኤጅንሲዎች ሁሉ መደበኛ አሠራር ነው።
- ምርመራዎች - አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሜትሮፖሊታን የፖሊስ ዲፓርትመንት፣ ከእሳት አደጋና ከድንገተኛ የህክምና አገልግሎት ክፍሎች፣ ከታክስና ገቢዎች ቢሮ፣ የተጠቃሚዎችና ቁጥጥር ጉዳዮች እና ሌሎችም ጋር በመሆን የቁጥጥርና የስምምነት አፈፃፀምና ለአካለ መጠን ያልደረሱ የመጠጥ ህግ ማክበር ምርመራዎችን ያካሂዳል። ይህ ፕሮግራም የተለያዩ ከፈቃድና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ጋር የተገናኙ ምርመራዎችን እንደ የመጨረሻ ህግ መከበርን፣ ፖስተሮችን፣ የተለዩ ሁኔታዎችን እና የሂሳብ ቁጥጥር ምርመራዎችን ያካሂዳል። እንቅስቃሴዎቹ በሙሉ የሚመለከታቸው የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ሕጎችንና ድንጋጌዎችን ለማወቅና ለማጠናከር ያገለግላሉ።
- ፈቃድ መስጠት - በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የአልኮል መጠጥ በማምረት፣ በማከፋፈል፣ በመሽጥ፣ ወይም በማስተናገድ ላይ ላሉ መጠጥ መሽጫዎች፣ ግሮሰሪ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች እና ለሌሎችም አዲስ የመጠጥ ፈቃድ መስጠትና ለነባር ፈቃድ የማደስ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም ሁሉንም ፈቃድ የመስጠት እንቅስቃሴዎችን ትክክለኛና በቀላል መገኘት የሚችሉ ወረቀትና የመረጃ መዝገቦች መያዝ እንዲቻል ከመዝገቦች አስተዳደር ጋር በመሆን ይሠራል። ይህ ፕሮግራም በቀጥታ ለጠቅላላ ህብረተሰቡ፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ለANCዎች እና ለማህበረሰብ ቡድኖች የደንበኞች አገልግሎቶች ይስጣል።
- የመዝገቦች አስተዳደር - ማህደሮችን፣ ዶክመንቶችን እና የዳታቤዝ መረጃን ለABRA ሠራተኛ፣ ለABC ቦርድና ለጠቅላላው ህብረተሰብ በመስጠት ትክክለኛውን መረጃና ማህደሮችን እንዲያገኙ ያስችላል። በተጨማሪም ፕሮግራሙ የማረጋጋጫ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ መረጃ በነፃነት የማግኘት ድንጋጌ ምላሽ መስጠትና ክትትል ያደርጋል እንዲሁም ለመጥሪያ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል።
የማስተርጎም አገልግሎቶች:
ABRA የተለየ እርዳታና የቋንቋ ትብብር አገልግሎቶችን (የመተርጎም ወይም የማስተርጎም) ያለ ምንም ክፍያ ይሰጣል። የተለየ እርዳታ ወይም የቋንቋ እርዳታ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን በስልክ ቁጥር 202.442.4423 ያነጋግሩን።
አድራሻ:
Alcoholic Beverage Regulation Administration
2000 14th Street, NW, Suite 400S
Washington, DC 20009
202-442-4423 – main #
202-442-9563 – fax #
[email protected]